የዚምባቡዌው አፍሪካን ናሽናል ዩኒዬን – ፓትሮይቲክ (ዛኑ ፒኤፍ) ፓርቲ የብሔራዊ ውጭ ግንኙነት ጸሃፊ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍኤም ሲ) ጸሃፊው ሲምባራሼ ሙቤንጌግዊ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖ እና የመንግስት ኮሙኒኬሸን ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ናቸው ለጸሃፊው አቀባበል አድርገውላቸዋል።፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
በጉባዔው ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡