በአሜሪካ በአውሮፕላንና ሄሊኮፕተር ግጭት እስካሁን የ19 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ አውሮፕላን እና ሄሊኮፕተር አየር ተጋጭተው በተፈጠረ አደጋ እስካሁን የ19 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
እንደ አሜሪካ አቪዬሽን አስተዳደር መረጃ÷ አውሮፕላኑ 60 መንገደኞችን እና አራት የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሲሆን ፥ ሄሊኮፕተሩ ደግሞ ሦስት ወታደሮችን ጭኖ ነበር፡፡
ምክንያቱ በውል ባልታወቀ እክል በተፈጠረ የአውሮፕላኑና የሄሊኮፕተሩ የአየር ላይ ግጭት አሰቃቂ አደጋም በርካቶች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተሰግቷል፡፡
አደጋውን ተከትሎ የመንገደኞች አውሮፕላን ፖቶማክ በተሰኘ ወንዝ ውስጥ በመግባቱ የሕይወት አድን ጀልባዎች እና ጠላቂዎች የነፍስ አድን ሥራ እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡
እስካሁን በተከናወነ ሥራም የ19 ሰዎችን አስከሬን አውሮፕላኑ ከወደቀበ ወንዝ ማውጣት መቻሉን ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል፡፡