Fana: At a Speed of Life!

የሩዋንዳ ፓትሪዮቲክ ፍሮንት (አር ፒ ኤፍ) ዋና ፀሐፊ ዌለርስ ጋሳማጌራ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የሩዋንዳ ፓትሪዮቲክ ፍሮንት (አር ፒ ኤፍ) ዋና ፀሐፊ ዌለርስ ጋሳማጌራ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ዋና ፀሐፊው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቱሪዝም ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

በጉባዔው ላይ ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

ጉባዔው በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማምጣት ራዕይን ለማሳካት የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይተላለፉበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፓርቲው 15 ነጥብ 7 ሚሊየን አባላት እንዳሉት ይታወቃል፡፡

በአለምሰገድ አሳዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.