በደቡብ ሱዳን በተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ የ20 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ሱዳን ዩኒቲ ግዛት አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ የ20 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።
አውሮፕላኑ ከግዛቷ ተነስቶ ወደ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ በማቅናት ላይ እያለ መከስከሱን የግዛቱ ኮሙኒኬሽን ሃላፊ ጋትዌች ባይፓል መግለጻቸውን ሬውተርስ ዘግቧል።
በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት የቻይናው ብሔራዊ ፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን እና የደቡብ ሱዳን መንግስት ተቋም የሆነው ናይል ፔትሮሊየም በጋራ የመሰረቱት ግሬተር ፐዮኔር ኦፕሬቲንግ ካምፓኒ ሰራተኞች መሆናቸውን ሃላፊው ተናግረዋል።
በተመሳሳይ በደቡብ ኮሪያ በደረሰ ሌላ የአውሮፕን አደጋ የቡሳን ኤይር ንብረት የሆነ አውሮፕላን በመንደርደያ ላይ እያለ የእሳት አደጋ ያጋጠመው ሲሆን በውስጡ የነበሩ 169 ተሳፋሪዎች እና ሰባት የበረራ ሰራተኞች በህይወት ለማትረፍ ተችሏል።
ከደቡብ ኮሪያ ጊማሃኤ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ወደ ሆንግ ኮንግ ለመብረር ሲያኮበኩብ አደጋው መድረሱ ተነግሯል።
በአውሮፕላኑ ውስጥ ከበነሩት ሰዎች ውስጥ ሶስቱ ብቻ መጠነኛ ጉዳት እንደገጠማቸው የዘገበው ስካይ ኒውስ፤ የተከሰተው የእሳት አደጋ መንስኤ እንዳልታወቀ ጠቅሷል።