Fana: At a Speed of Life!

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍን ያስደነገጠው ዲፕሲክ የሳይበር ጥቃት ደረሰበት

ይፋ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ ታዋቂነትን ያተረፈው የቻይና የቴክኖሎጂ ዲፕሲክ በደረሰበት የሳይበር ጥቃት ምክንያት አዳዲስ ተጠቃሚዎችን ለጊዜው መመዝገብ ማቆሙን አስታወቀ፡፡

የቴክኖሎጂ ዓለምን ያስደነገጠው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቻትቦት “ዲፕሲክ” በአገልግሎቶቹ ላይ “ትልቅ ተንኮል አዘል ጥቃቶች” ደርሶብኛል ብሏል።

አዲስ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴል የሆነው ዲፕሲክ ለተጠቃሚዎች ከተዋወቀ በኋላ የቴክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከፍተኛ ትኩረት አግኝቷል።

ኩባንያው የቻትጂፒቲ ፈጣሪ ከሆነው እንደ ኦፕን ኤአይ ካሉ የአሜሪካ ኩባንያዎች ጋር ተወዳዳሪ እንደሆነም ነው የገለጸው።

ይህንን ተከትሎ በርካታ ተጠቃሚዎችን ያፈራው መተግበሪያ በደረሰበት የሳይበር ጥቃት ምክንያት አዳዲስ ተመዝጋቢዎችን መቀበል ማቆሙን አስታውቋል፡፡

ኩባንያው ቀድመው የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች ወደ ድረገጹ ለመግባት ሲያጋጥማቸው የነበረውን ችግር አንደፈታም አመልክቷል፡፡

ዲፕሲክ በቻይና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተሰራ ሲሆን ከቻት ጂፒቲ እና መሰል ተወዳዳሪዎቹ ጋር ሲነጻጸር እጅግ ባነሰ ዋጋ በመሰራቱና አገልግሎት መስጠት በመቻሉ ተፈላጊነቱን ከፍ አድርጎለታል ተብሏል።

ይህ የአሜሪካውን ሲሊከን ቫሊ ያስደነገጠው ዲፕሲክ ዶናልድ ትራምፕን ሰይቀር ማስደመሙ አልቀረም።

ፕሬዚዳንቱ “ለዘርፉ የማንቂያ ደወል ነው” በማለት በአገራቸው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ የሚሰሩ ኩባያዎች አሰራራቸውን እንዲያሻሽሉም ተናግረዋል።
ዲፕሲክ በዘርፉ ያገኘው ደማቅ አቀባበልና ተወዳጅነት አሜሪካ በቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ ያላትን አተያይ መልሳ እንድታጤን ሳያደርጋት አይቀርም ተብሏል።

በዚህም የዲፕሲክ በአፕል ኩባንያ አፕስቶር ተጠቃሚዎች በብዛት አውርደው የተጠቀሙት መተግበሪያ በመሆን በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን የፎርብስ መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.