የሰሞኑ የአየር ሁኔታ በውሃ ዘርፍ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ …
አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጥር ሊኖር የሚችለው መጠነኛ እርጥበት ለውሃ ሀብት መሻሻል አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
ከሰኞ ጀምሮ ለ11 ቀናት አብዛኛው የአፋር ደናክል፣ ዋቢ ሸበሌ፣ ገናሌ ዳዋ፣ መረብ ጋሽ፣ ኦጋዴን፣ አይሻ፣ ባሮ አኮቦ፣ አባይ እንዲሁም የተከዜ ተፋሰሶች በደረቅ ሁኔታ ስር ይቆያሉ ተባለ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በመጨረሻዎቹ ጥቂት ቀናት በላይኛው እና በመካከለኛው ስምጥ ሸለቆ፣ በጥቂት ላይኛው ኦሞ ጊቤ እና አዋሽ ተፋሰሶች ላይ መጠነኛ እርጥበት ያገኛሉ፡፡
ጥር የበጋ ወቅት ማብቂያ እንዲሁም የበልግ ወቅት መሸጋገርያ ወር በመሆኑ ሊኖር የሚችለው መጠነኛ እርጥበት በጥቂቱም ቢሆን ለውሃ ሀብት መሻሻል አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያመላክታል፡፡