Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራው በሀገሩ እየተመዘገበ ላለው እድገት ሚናውን ሊወጣ ተዘጋጅቷል – ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዳያስፖራው በሀገሩ እየተመዘገበ ላለው እድገትና ልማት የበኩሉን ሚና እንዲጫወት በልዩ ሁኔታ መዘጋጀቱን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ በኒውዮርክ እና አካባቢው ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚህም የታደሰው የብሔራዊ ቤተ-መንግስት ሙዝየም የኢትዮጵያን ታሪክ ጥልቀትና እና ስፋት የሚመሰክር ነው ሲሉ እንደገለጹላቸው አስፍረዋል፡፡

ዳያስፖራዎች በሀገራቸው እየተመዘገበ ላለው እድገትና ልማት የበኩላቸውን ሚና ለመጫወት በልዩ ሁኔታ መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.