በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውይይት ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚደረግ የንቅናቄ ውይይት ተጀምሯል፡፡
ውይይቱ የሚካሄደው “ብሔራዊ ጥቅሞቻችን እና ቀጣናዊ ትስስር ለሚዛናዊ የሕዝቦች ተጠቃሚነት’’ በሚል መሪ ሃሳብ ነው፡፡
ዓላማው የኢትዮጵያን ቀጣናዊ ትስስር ብሔራዊ ጥቅሞቿን ባማከለ መልኩ በማጠናከር ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት ነው ተብሏል፡፡
ለዚህም በሚደረጉ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥናታዊ ጽሑፎች እያቀረቡ ውይይት በማድረግ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ግንዛቤ እንደሚፈጠርም ተጠቁሟል፡፡
በሰላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት የሚደረገው ይህ ሀገራዊ ንቅናቄ 129ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ከመከበሩ በፊት እስከ የካቲት 20/2017 ዓ.ም የሚጠቃለል እና በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሚካሄድ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡