Fana: At a Speed of Life!

ኃብትን መጠበቅና ማልማት ልዩ ትኩረት የምንሰጠው ብርቱ ጉዳያችን ነው- አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ኃብትን መጠበቅና ማልማት ልዩ ትኩረት የምንሰጠው ለህዝባችንም ቃል የገባነው ብርቱ ጉዳያችን ነው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ያሉን ፀጋዎችና ኃብቶች ከነበሩባቸው የህልውና ስጋት በመጠበቅና በመንከባከብ ብሎም እሴት ጨምረን በማልማት ለአሁኑና ለቀጣዩ ትውልድ ተምሳሌት የሚሆኑ ስራዎችን መስራታችን ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የታሪካዊ ከተማችን የጎንደር ከተማ የኮሪደርና የፋሲል አብያተ መንግስታት እድሳትም ለዚህ ህያው ምስክር ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በእምቅ ባህላዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ ኃብቶች የተከበበችውን ጎንደር ከተማ ቀይዶ የያዛትን መልከ ብዙ አሚኬላዎችን ሁሉ እየነቀልን፣ አቧራ የለበሱ ኃብቶቿን ሁሉ እየገለጥን የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት እሴት ቀጠና እንድትሆን በትጋት እንሰራለንም ነው ያሉት፡፡

ሌሎች ከተሞች ላይ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል፡፡

ለህዝባችን የምንፈፅመውን ብቻ ቃል የመግባት፣ የመጀመርና የማጠናቀቅ ልምምዳችንን ባህል እያደረግን፤ እዛው ሳለም ለሀገራችን ምጣኔ ኃብታዊ እና ማህበራዊ ልማት በሚውል አግባብ ይከናወናል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.