Fana: At a Speed of Life!

የምንሰራው ስራ የሀገራችንን ዘላቂ ልማትና ሰላም የሚያረጋግጥ ነው – ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምንሰራው ስራ የኢትዮጵያን ዘላቂ ልማትና ሰላም የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

“ከቃል እስከ ባህል!” በሚል መሪ ሃሳብ በመዲናዋ ሲካሄድ የቆየው የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንስ የማጠቃለያ መድረክ ተከናውኗል፡፡

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስስር ገጻቸው ፥ ፓርቲው ኢትዮጵያን የማበልጸግ ራዕይ ሰንቆ ከየትኛውም ዋልታ ረገጥ እሳቤ ርቆ ሚዛናዊ የመሃል ፓለቲካ እሳቤን በመከተል ተግባቦት ላይ የተመሰረተ የዳበረ የዴሞክራሲ ባህልን መገንባት፣ አካታችና ሰው ተኮር ስራዎችን በመተግበር የኑሮ ጫና የሚያቀሉ ስራዎችን በመስራት ቃልን በተግባር እየፈፀመ ያለ ግዙፍ ፓርቲ ነዉ ብለዋል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ አልፎ እስከዛሬ ድረስ በሀገር ውስጥና በውጪ የተመዘገቡ ድሎችን የተጎናፀፈው በፅናት እየተራመደ ከህዝብ ጋር በትብብር በሰራው ስራ ነውም ብለዋል።

በተገባው ቃል መሰረት አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና አዲስ ለማድረግ 24/7 በመስራት የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት የሚረጋግጡና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርጓት አስደናቂ ስራዎች መከናወናቸውንም አንስተዋል።

የምንሰራው ስራ የሀገራችንን ዘላቂ ልማትና ሰላም የሚያረጋግጥ በመሆኑ በቀጣይም ከህዝብ ጋር በመሆን የኢትዮዽያን ብልፅግና ለማረጋገጥ ተግተን መስራታችንን አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናልም ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.