ሃሰተኛ መረጃ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በካናዳ የሥራና ትምህርት ዕድል ለማመቻቸት ሕጋዊ ውክልና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር) የተሰጣቸው በማስመሰል ሕገ ወጥ ደብዳቤ አዘጋጅተው እያሰራጩ ያሉ አካላት መኖራቸውን አስታውቋል፡፡
የሚኒስትሩ ስም ተጠቅሶ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወረ የሚገኘው ደብዳቤ ሃሰተኛ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አረጋግጧል፡፡
መሰል የወንጀል ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ሕብረተሰቡም ይህንን ተገንዝቦ ራሱን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡