Fana: At a Speed of Life!

የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሕንፃ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባለ 13 ወለል ያለውን የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ሕንፃ ግንባታ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ ግንባታው ዘመኑን የሚመጥን የስራ አካባቢ ለመፍጠር በተለያዩ አካባቢዎች ተበታትነው ሲሰጡ የነበሩትን አገልግሎቶችን ወደ አንድ ማእከል በማሰባሰብ አገልግሎት የሚያሳልጥ ነው ብለዋል፡፡

እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች ምቹ፣ የአገልጋይና የተገልጋይ እንግልትን የሚቀንስ፣ ስማርት ሲቲን የመፍጠር ግብን ለማሳካት የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ተካትተውበት የተገነባ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በውስጡ 120 ቢሮዎችን ጨምሮ እያንዳንዳቸው 1 ሺህ 500 እና 500 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ሁለት የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ በቂ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ ጂምናዚየም፣ የሕፃናት ማቆያና መጫወቻ ቦታ እና መሰል መገልገያዎች ያሟላ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ከንቲባዋ “ለህዝብ በገባነው ቃል መሰረት በጥራት ገንብተን ያጠናቀቅነው ይህ ህንፃ ውጪን በመቆጠብ ከዚህ በፊት ለቢሮ ኪራይ የምናውለውን ሀብት በማስቀረት ለልማት እንድናውል ያስችለናል” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.