አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሳዑዲ አምባሳደር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር ፋሃድ ኦባይዳላህ አልሁማይዳኒ አልሞታይሪ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም የኢትዮጵያ እና የሳዑዲ አረቢያን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነቶችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል።
እንዲሁም የሀገራቱ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች በየሀገራቱ የሥራ ጉብኝት ማድረግ የሚችሉበትን ሁኔታ መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።