Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል እና ሃማስ የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እስራኤል እና ሃማስ ሳምንታትን ከፈጀ ድርድር በኋላ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተሰምቷል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱ በዙር እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን የመጀመሪያው ዙር ለስድስት ሳምንታት ይቆያል ተብሏል፡፡

በዚሁ መሠረት በመጀመሪያው ዙር ስምምነት ሃማስ 33 ታጋቾችን እንዲሁም እስራኤል 1 ሺህ የሚጠጉ ፍልስጤማውያንን ለመልቀቅ መስማማታቸውን ፍራንስ 24 ዘግቧል።

የሁለቱ ወገኖች ስምምነት ለ15 ወራት የዘለቀውን የጋዛ ጦርነት መፍትሔ እንደሚያበጅለት ይጠበቃል ተብሏል፡፡

ስምምነቱ  አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ኳታር፣ ግብጽ እና አሜሪካ በማደራደር እና በድጋፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ተገልጿል፡፡

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ “በመካከለኛው ምሥራቅ ታጋቾች ይለቀቃሉ፤ ከስምምነትም ተደርሷል” ብለዋል፡፡

ስምምነቱ በሃማስ በኩል ዕውቅና ያገኘ ሲሆን÷ በእስራኤል በኩልም ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ እንደሚያጸድቁት እና መንግሥታቸውም ነገ ድምጽ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.