Fana: At a Speed of Life!

ከጣልያን እና ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ኩባንያዎች ጋር በጋራ ለመስራት ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከጣልያኑ ማይንድ እና ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሪች ግሩፕ ኩባንያዎች ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ የስራ ሃላፊዎች ከጣሊያኑ ማይንድ (ሚላን ኢኖቬሽን ዲስትሪክት) ኩባንያ ተቋማዊና ኢንተርናሽናል ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አልቤርቶ ሚኖ ጋር በትብብር ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ መክረዋል።

የፓርኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሔኖክ አህመድ ፥ ከጣሊያኑ ማይንድ ግዙፍና ብዙ ዓለም አቀፍ አጋር ካለው ኩባንያ ጋር የሚደረግ የትብብር ስራዎችን በአጭር ጊዜ ወደ ስራ ለማስገባት እንሰራለን ብለዋል።

አልቤርቶ ሚኖ እንዳሉት÷ኩባንያቸው ከኢትዮጵያ ጋር በቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይል ግንባታ፣ በስታርታፕ፣ በምርምርና በሌሎች ዘርፎች ላይ በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ ጠቁመዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በተባበሩት አረብ ኤምሬት የኢትዮጵያ አምባሳደር ኡመር ሁሴን(ዶ/ር) የተመራው የተባበሩት አረብ ኤምሬት ሪች ግሩፕ ካምፓኒ ጋር በኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ፣ ዲጂታልና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ በጋራ ለመስራት ምክክር አካሂደዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር)÷ ሀገራዊ የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለማጎልበት የሚያስችሉ ምቹ ስነ-ምህዳርን በመፍጠር ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አስገንዝበዋል፡፡

አምባሳደር ኡመር ሁሴን(ዶ/ር)÷ የኢትዮጵያ መንግስት በቴክኖሎጂ፣ ለዲጂታልና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው ኩባንያው በጋራ ለመስራት ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱም ወሳኝ ሚና እንዳለው ማንሳታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.