Fana: At a Speed of Life!

ቢስት ባር የመደመር እሳቤ በተግባር የሚገለጽበት በዓል ነው – ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)”ቢስት ባር “የመደመር እሳቤ በተግባር የሚገለጽበት በዓል ነው ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርእሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር ኢ/ር)ተናገሩ፡፡

የቤንች ብሔር ዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቢስት ባር” ማጠቃለያ መርሐ ግብር በሚዛን አማን ከተማ ተካሂዷል።

በበዓሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርእሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር ኢ/ር)፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋነሽ ኬሌሮ፣ የፌደራልና የክልል የስራ ሀላፊዎች፣ የቤንች ብሔር የጎሳ መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም ታድመዋል።

ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ በቢስት ባር በዓል የብሔሩ አባላት ተሰብስበው በአብሮነት የሚያሳልፉትና መጪውን አዲስ የመደመር አስተሳሰብ በተጨባጭ የሚገለጽበት ነው ብለዋል።

ይህ ድንቅ ባህል ተጠንቶና ተሰንዶ ለትውልዱ ሊተላለፍ ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ የብሔሩ ምሁራን ማህበረሰቡ ያዳበረውን ቱባ የባህል እሴት ለሰላምና ለዕድገት እንዲውል በማድረግ ሁሉም የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን÷ የለውጡ መንግስት ለባህል በሰጠው ትኩረት በርካታ ቱሪስቶች አካባቢው እየጎበኙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቢስት ባር ለበኩር ቅድሚያ የሚሰጥበት፣ መተሳሰብ ፣ መደማመጥ ያለበት ድንቅ በዓል ነው ያሉት አስተዳዳሪው ይህንን በዓል ለቀጣይ ትውልድ ጠብቆ የማቆየት ሃላፊነት አለብን ነው ያሉት፡፡

በተስፋዬ ምሬሳ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.