Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ጫልቱ በምስራቅ አፍሪካ የዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በምስራቅ አፍሪካ የተባበሩት መንግስታት የሰፈራ ፕሮግራም (ዩኤን ሃቢታት) ዋና ዳይሬክተር ኢሻኩ ሜቱምቢ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷በኢትዮጵያና በቀጣናው ሀገራት በተከናወኑ ሥራዎችና መልካም ተሞክሮዎች ዙሪያ መምከራቸውን አንስተዋል፡፡

የተመድ የአሰፋፈር ፕሮግራም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምና ሀገራዊ የልማት ስትራቴጂ እቅድ ጋር ያለውን ተስማሚነት በተመከተ መወያየታቸውንም ተናግረዋል፡፡

በዚህም በሀገራዊ፣ ቀጣናዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ነው የገለጹት፡፡

ኢትዮጵያ በቀጣይ መጋቢት ወር ለተመድ የዘላቂ የአሰፋፈር ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ለምታቀርበው የመልካም ተሞክሮና የከተማ ልማት የመሪነት ሚና ከወዲሁ ዝግጁት መጀመሯንም አስረድተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.