Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስና አርባ ምንጭ ከተማ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ14ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አርባ ምንጭ ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ ስሑል ሽረን ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ በፍጽም ጥላሁን ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ምሽት 12 ሰዓት በተከናወነው ሌላኛው መርሐ ግብር ደግሞ አርባ ምንጭ ከተማ በአሕመድ ሁሴንና በፍቅር ግዛው ግቦች አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.