Fana: At a Speed of Life!

በኮንትሮባንድ ሊታጣ የነበረ ከ107 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በንግድ ማጭበርበርና ኮንትሮባንድ መንግስት ሊያጣ የነበረውን ከ107 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉ ተገልጿል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ ባለፉት ስድስት ወራት በጉምሩክ ኮሚሽን በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸው ተመላክቷል።

በተለይም ኮንትሮባንድና ንግድ ማጭበርበርን በመከላከል ረገድ አመርቂ ውጤት መመዝገቡ ነው የተገለጸው፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ÷ባለፉት ስድስት ወራት 8 ነጥብ 95 ቢሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን አስረድተዋል።

በኮንትሮባንድ ዝውውር የተጠረጠሩ 708 ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው አስፈላጊው ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው እየተደረገ ነው ማለታቸውንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

በግማሽ ዓመቱ በንግድ ማጭበርበር እና በኮንትሮባንድ መንግስት ሊያጣው የነበረ 107 ነጥብ 24 ቢሊየን ብር ማዳን መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.