የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ለአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ለአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የተለያዩ መድሀኒቶች ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉ የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ጉድ ኔበርስ ከተባለ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር የተሰጠ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡
የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በጤናው ዘርፍ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ሲሆን፤ ለጤና ዘርፍ የመሳሪያ እና የመድሃኒት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ከፅህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡