Fana: At a Speed of Life!

የምድር ባቡር ወደ ስኬት እየተጓዘ ነው- ታከለ ኡማ (ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮ-ጂቡቲ ምድር ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር በስኬት ጎዳና ላይ እንደሚገኝ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) ገለጹ፡፡

ባለፉት ወራት የተመዘገበው ስኬት በትክክለኛ መንገድ ላይ መሆኑን እንደሚያመላክት ተቋሙ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በላከው መረጃ አስታውቋል፡፡

የተመዘገበው አበረታች ውጤትም በቀጣይ ዓመታት ተቋሙን ትርፋማ ለማድረግ ለተቀመጠው ዕቅድ መነሻ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ለተመዘገበው ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱት የባቡር መንገዱ ሠራተኞችም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.