Fana: At a Speed of Life!

የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ “ቢስት ባር” እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ “ቢስት ባር” የቤንች ብሄር መነሻ እንደሆነ በሚታመንበት ስፍራ “ዣዥ” ቀበሌ በድምቀት እየተከበረ ነው።

የቤንች ብሔር ዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል የሆነው ቢስት ባር የበኩር እህል የሚቀመስበትና ከክረምት ወንዝ ሙላትና ጨለማ መሻገርን ምክንያት በማድረግ ምስጋና የሚቀርብበት በዓል ነው።

ለታላላቆች ክብር መስጠት፣ መደማመጥ፣ አብሮነት፣ እርቅና ሰላም የቢስት ባር በዓል መሠረቶች ናቸው።

በዓሉ ከረጅም ጊዜ መቋረጥ በኋላ ባለፈው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ መከበር መጀመሩ ይታወሳል።

በተስፋዬ ምሬሳ እና ዘርያዕቆብ ያዕቆብ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.