ከ451 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት 6 ወራት ከ451 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማውን በቢሾፍቱ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ ሚኒስትሯ ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ÷ በተያዘው በጀት አመት ተቋሙ በ”ግብር ለሀገር ክብር “ንቅናቄ ከቢሊየን ወደ ትሪሊየን ገቢ ስኬት የሚያደርገው ጉዞ ስኬታማ እየሆነ መምጣቱን ገልፀዋል።
በተያዘው በጀት አመት 6 ወራትም 445 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 451 ነጥብ 4 ቢሊየን ወይም የእቅዱን 101 በመቶ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አንስተዋል፡፡
ገቢውም ከሀገር ውስጥ ታክስ እና ከጉምሩክ ቀረጥና ታክስ የተሰበሰበ መሆኑን አመላክተዋል።
የ6 ወራት አፈፃፀሙ ጥሩ የሚባል ቢሆንም በቀሪ ወራት የዓመቱን እቅድ ለማሳካት ሊሰራ እንደገሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በዳዊት ጎሳዬ