በጎንደር ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ አዳሪ ት/ቤት ሊገነባ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጎንደር ከተማ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለሚገነባው ዘመናዊ አዳሪ ት/ቤት 225 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡
የአደሪ ት/ቤቱ ግንባታ በሶስት ምዕራፍ የሚከናወን ሲሆን÷ለመጀመሪያው ምዕራፍ 600 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡
ለት/ቤቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታም ዳሽን ቢራ ፋብሪካ 225 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን አስታውቋል፡፡
ፋብሪካው በቀጣይ በተለያዩ ዘርፎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ያረጋገጠው፡፡
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው በበኩላቸው÷ ፋብሪካው በከተማዋ የትምህርት ተቋማትን ለመቀየር በሚደረገው ጥረት አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ለአዳሪ ት/ቤቱ ግንባታ የሚውል 4 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት ማዘጋጀቱንም ጠቁመዋል፡፡
በምናለ አየነው