ድሬ ሀሪፍ ሀገር አቀፍ የብስክሌት ውድድር ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከታሕሣሥ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በድሬዳዋ ሲደረግ የቆየው ድሬ ሀሪፍ ሀገር አቀፍ የብስክሌት ውድድር የማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ ከአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ትግራይ እና ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ የተውጣጡ 36 የከፍተኛ ኮርስ ብስኪሌተኞች ተሳትፈዋል፡፡
80 ኪሎ ሜተር በሸፈነው የፍጻሜ ውድድር ዐቢይ አለም ከወልዋሎ አዲስ መድሃኒት ፋብሪካ አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡
በቡድን ወልዋሎ አዲስ መድሃኒት ፋብሪካ የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን÷ድሬዳዋ ከተማ እና ቶቶ የብስክሌት ክለብ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል።
የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ወንድሙ ሃይሌ÷ ውድድሩ ተተኪዎችን ለማፍራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል፡፡
መርሐ ግብሩ በቀጣይ ሀገር ለሚወክሉ ስፖርተኞች ያሉበትን ደረጃ እንዲያዩ እድል ይሰጣልም ነው ያሉት፡፡
በሰለሞን በቀለ