Fana: At a Speed of Life!

የኦክስጂን ማምረቻ ፋብሪካ ተመርቆ ሥራ ጀመረ

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የይርጋዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ የኦክስጂን ማምረቻ ፋብሪካ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በተገኙበት ተመርቆ ሥራ ጀምሯል።

ፋብሪካው 86 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን÷ በቀን ከ190 በላይ በባለ 50 ሊትር ሲሊንደር ኦክስጂን ማምረት ይችላል ተብሏል።

ሆስፒታሉ ከሚያመርተው ኦክስጂን ለራሱ ተጠቅም ለሌሎች 10 የአካባቢው ሆስፒታሎች ማቅረብ የሚቻለው መሆኑም ተጠቁሟል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ከዶክተር መቅደስ ዳባ እና ከአቶ ደስታ ሌዳሞ በተጨማሪ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ እና ሌሎች የክልሉና የፌዴራል የአመራር አባላት ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.