Fana: At a Speed of Life!

በዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እስከ 10 ደረጃን በመያዝ አሸነፉ

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ ድል አስመዘገቡ።

 

ከማለዳው 11 ሰዓት ጀምሮ በዱባይ በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያውያኑ የተሰጣቸውን ቅድሚያ ግምት አሳክተዋል።

 

በዚህም በሁለቱም ጾታ ከአንደኛ እስከ አስረኛ ድረስ ያለውን ደረጃ በመያዝ በፍጹም የበላይነት ውድድሩን አጠናቅቀዋል።

 

ውድድሩን በሴቶች አትሌት በዳቱ ሂርጳ 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ27 ሴኮንድ በመግባት በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ፥ አትሌት ደራ ዲዳ እና አትሌት ትዕግስት ግርማ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

 

በወንዶች ደግሞ አትሌት ቡቴ ገመቹ 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ50 ሴኮንድ በርቀቱ የዓመቱን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አንደኛ ወጥቷል።

 

አትሌት ብርሃኑ ፀጉና አትሌት ሽፈራው ታምሩ ደግሞ  ሁለተኛና ሶስተኛ ወጥተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.