ከ175 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ
አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ175 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን ገለፀ፡፡
ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እፅ፣ መድኃኒት እና የውጭ ሀገራት ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡
ከታህሳስ 25 እስከ ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ሞያሌ፣ አዳማ እና አዋሽ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ መያዛቸው ተመላክቷል፡፡
የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 23 ተጠርጣሪ ግለሰቦች እና 11 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡