Fana: At a Speed of Life!

ሀድያ ሆሳዕና እና ፋሲል ከነማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀድያ ሆሳዕና እና ፋሲል ከነማ አንድ አቻ ተለያዩ፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ብሩክ በየነ ለሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም ማርቲን ኪዛ ለፋሲል ከነማ ግቦቹን አስቆትረዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ሀድያ ሆሳዕና የሊጉን መሪነት ለመቻል ሲያስረክብ በአንፃሩ የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ቡድን ፋሲል ከነማ ነጥብ በመጋራት ሶስት ደረጃዎችን ማሻሻል ችሏል፡፡

የሊጉ 13ኛ ሳምንት መርሃ ግብሮች መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ መድን ይገናኛሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.