Fana: At a Speed of Life!

ኦሮማይ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ ተተረጎመ

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የበዓሉ ግርማ ታላቅ ድርሰት የሆነው “ኦሮማይ” ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ መተርጎሙ ተሰማ።

መፅሀፉን ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ የተረጎሙት ዴቪድ ደ ጉስታ እና መስፍን ፈለቀ ይርጉ መሆናቸው ታውቋል።

በ1970ዎቹ መቼቱን ያደረገው ኦሮማይ በስነ-ፅሁፍ ስልቱና በይዘቱ የተዋጣለት ድርሰት መሆኑን በርካታ ደራሲያንና ሃያሲያን መስክረውለታል።

መፅሀፉ ለደራሲው በዓሉ ግርማ መገደል ምክንያት መሆኑ ይነገራል።

በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተተረጎመው ኦሮማይ 400 ገፅ ያለው ሲሆን በእንግሊዝ ሀገር መታተሙን ጋርዲያን ካወጣው መረጃ ተመልክተናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.