Fana: At a Speed of Life!

አማራ ክልልን ከጎበኙ ቱሪስቶች ከ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ሥድስት ወራት የተለያዩ መዳረሻዎችን ከጎበኙ ቱሪስቶች 2 ቢሊየን 541 ሚሊየን 906 ሺህ 197 ብር መገኘቱን የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡

11 ሺህ 158 የውጭ እና 5 ሚሊየን 401 ሺህ 631 የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች በክልሉ ጉብኝት ማድረጋቸውን የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አበበ እምቢአለ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

በዚህም ከውጭ ቱሪስቶች 60 ሚሊየን 425 ሺህ 168 ብር እንዲሁም ከሀገር ውስጥ ጎብኝዎች 2 ቢሊየን 481 ሚሊየን 481 ሺህ 29 ብር መገኘቱን አብራርተዋል፡፡

ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ እና ተጠቃሚነት ለማሳደግ የክልሉ መንግሥት በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጥር ወር “ጥምቀትን በጎንደር” በልዩ ሁኔታ እንደሚከበር እና በተለያዩ አካባቢዎችም ልዩ ልዩ ሁነቶች እንደሚከናወኑ ጠቅሰዋል፡፡

የክልሉ እና የፌደራል ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ታዋቂ የኪነ-ጥበብ ሰዎች በተገኙበትም 16ኛው የአማራ ክልል የባሕልና ኪነ-ጥበብ ፌስቲቫል ከጥር 7 እስከ 9 በጎንደር ከተማ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.