Fana: At a Speed of Life!

በካሊፎርኒያ በተከሰተው ሰደድ እሳት የሟቾች ቁጥር 10 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከካሊፎርኒያ ጫካ ተነስቶ እስከ ሎስ አንጀለስ በዘለቀው ሰደድ እሳት ሕይዎታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 10 መድረሱ ተሰምቷል፡፡

በአካባቢው ያለው ከፍተኛ ነፋስ ሰደድ እሳቱ እንዲባባስ ማድረጉም ተገልጿል፡፡

አንድ የሎስ አንጀለስ ባለስልጣን እንዳሉት÷ ሰደድ እሳቱ ወደ ሌሎች አካባቢዎች የመዛመት እድሉ ከፍተኛ ነው፤ የሟቾች ቁጥርም ሊያሻቅብ ይችላል፡፡

ሰደድ እሳቱ  ምክንያት እስከ አሁን ከ5 ሺህ በላይ መዋቅሮች መውደማቸውም ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል አደጋውን እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ዘረፋ ሲፈጽሙ ነበር የተባሉ 20 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተጠቅሷል፡፡

እንዲሁም በሥራ ላይ የነበረች የእሳት አደጋ አውሮፕላን ከድሮን ጋር መጋጨቷን እና በዚህ አደጋ ጉዳት አለመድረሱን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.