ደቡብ ጎንደር ዞን የ24 ሚሊየን ብር የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አገኘ
አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ደቡብ ጎንደር ቅርንጫፍ ለእስቴ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት 24 ሚሊየን ብር የሚገመቱ የመድኃኒትና የህክምና አገልግሎት መስጫ ማሽኖችን ድጋፍ አድርጓል፡፡
የእስቴ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ውለታው ጌጤ በርክክብ ሥነ-ስርዓቱ እንደገለጹት÷ ሰብዓዊ ድጋፉ የ24 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የመድኃኒትና የህክምና አገልግሎት መስጫ ማሽኖችን ያካተተ ነው፡፡
በድጋፍ የተገኘው መድኃኒት በወረዳው ለሚገኙ ጤና ጣቢያዎች እንደሚከፋፈልና ለማህበረሰቡ በነፃ አገልግሎት የሚሰጥ እንደሆነም መናገራቸውን የወረዳው ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡