Fana: At a Speed of Life!

በባቱ ከተማ የጥምቀት በዓልን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ተደርጓል

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ባቱ ከተማ የጥምቀት በዓልን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

በከተማዋ የጥምቀት በዓልን በደምበል ደሴቶች በድምቀት ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉ ነው የተመላከተው፡፡

በከተማዋ የሚከበረው የጥምቀት በዓል ለቱሪዝም ዘርፉ መነቃቃት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በበዓሉ ለመታደም ወደ ከተማዋ የሚመጡ እንግዶች አስፈላጊውን አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሰራ እንደሆነም ተገልጿል።

በዓሉ በደምበል ደሴቶች በሚከበርበት ወቅት ለመጓጓዣነት የሚያገለግሉ አነስተኛ ጀልባዎች መዘጋጀታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የክልሉ መንግስት ከተሞችን በማልማት የቱሪስት መዳረሻነታቸውን ለማስፋፋት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.