Fana: At a Speed of Life!

በላሊበላ ከተማ የገና በዓል በድምቀት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በላሊበላ ከተማ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና) ከዋዜማው ጀምሮ ሃይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ በድምቀት ተከበረ።

ዛሬ በተጠናቀቀው በዓል ላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች የታደሙ ሲሆን፤ ሂደቱም የተሳካና ላሊበላ ከተማን ያደመቀ እንደነበር ተነግሯል።

በዓሉ በድምቀትና በስኬት እንዲጠናቀቅ የአካባቢው ነዋሪዎች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር በመሆን በጋራ በመስራት አስተዋጽኦ አድርገዋል።

በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ነጋ ድንበሩ እንደገለጹት፤ ሥነ-ሥርዓት በማስከበር የበዓል ማክበር ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ማደረግ ተችሏል።

ታዳሚዎች በዓሉን ያለምንም ችግር ማክበር እንዲችሉ የፀጥታ ሃይሉ ወጣቶችን ያሳተፈ ወንጀልን የመከላከልና ሰላም የማስክበር ስራ ማከናወኑን ተናግረዋል።

ለዚህም ከዋዜማው ጀምሮ በተከናወነ የተቀናጀ ስራ በዓሉ በድምቀትና በስኬት ተከብሯል ብለዋል።

በበዓል አከባበሩ በተራ ሌብነት ተሰማርተው የተገኙ ሦስት ግልሰቦች መያዛቸውንና በጊዜያዊነት ለተቋቋመው ችሎች ቀርበው ውሳኔ እንዲያገኙ መደረጉን መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.