Fana: At a Speed of Life!

ጤና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ በመቄዶኒያ ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጤና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር ለተጠለሉ ወገኖች ማዕድ አጋርተዋል፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና የተቋሙ የሥራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች በዓሉን በማስመልከት መቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበርን በመጎብኘት ማዕድ አጋርተዋል።

ከማዕድ ማጋራቱም ባለፈ የንጽሕና መጠበቂያ፣ የመድኃኒትና ሌሎችንም ድጋፎችን አድርገዋል።

ከጉብኝቱ በኋላ ዶክተር መቅደስ ዳባ÷ በገና በዓል በመቄዶኒያ በመገኘት ማዕድ በማጋራታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ተቋማቸው ለአረጋዊያኑ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየቱን አስታውሰው በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።

በጤና ሚኒስቴር የመድኃኒት፣ የአምቡላንስና ሌሎችም ድጋፎች ሲደረጉ እንደነበር በመግለጽ በቀጣይም የተጠናከረ ድጋፍ ይደረጋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በ44 ቅርንጫፎች ከ8 ሺህ በላይ ወገኖችን እየደገፈ መሆኑ ይታወቃል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.