በርዕደ መሬት የ95 ሰዎች ሕይዎት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ቻይና ቲቤት ግዛት 7 ነጥብ 1 ሬክታር ስኬል የተመዘገበ ርዕደ መሬት የ95 ሰዎችን ሕይዎት ሲቀጥፍ ከ130 በሚልቁት ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡
ርዕደ መሬቱ ከ10 ኪሎ ሜትር በላይ ጥልቀት እንዳለው እና ሺጋትሲ በተባለችው የቲቤት አካባቢ ሌሊት 7 ሠዓት ገደማ መከሰቱን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡
ከ1 ሺህ 500 በላይ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች መሠማራታቸውን እና የነፍስ አድን ሥራው መቀጠሉም ተመላክቷል፡፡
መጠነ ሰፊ የነፍስ አድን ሥራ እንዲደረግ ያዘዙት የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ÷ በአደጋው የተፈናቀሉ ዜጎችም ወደ ተዘጋጀላቸው መጠለያ እንዲገቡ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡