አሥተዳደሩ በተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ማዕድ አጋራ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 29፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ለሚገኙ አቅመ ደካሞችና ለማኅበራዊ ችግሮች ተጋላጭ ወገኖች ማዕድ አጋራ፡፡
የማዕድ ማጋራት መርሐ-ግብሩ የተከናወነው የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ መሆኑን የአሥተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
በዓልን ከአቅመ ደካሞች ጋር አብሮ ማክበር እና የተቸገሩትን ደገፍ ነባር ኢትዮጵያዊ ባሕል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በከተማዋ በሚገኙ 22 የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት በዓሉን ከአቅመ ደካማ እና የሀገር ባለውለታ ወገኖች ጋር የማክበር መርሐ-ግብር እያከናወኑ እንደሚገኙም ጠቅሰዋል፡፡
በተመሳሳይ ከንቲባዋ ለሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሠራተኞች ማዕድ አጋርተዋል፡፡
የጣላችሁት መሠረት ለትውልድ የሚተላለፍ ደማቅ ታሪክ ነው ሲሉ በኮሪደር ልማቱ የተሳተፉ አካላትን አበረታትተዋል፡፡
በሰማኸኝ ንጋቱ