Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያን በአፍሪካ ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ነባር መዳራሻዎች ዓለም አቀፍ ደረጃን እንዲያሟሉ እየተደረገ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሯ በላሊበላ ከተማ የገና በዓል አከባበር ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የነበሩ የቱሪዝም መስኅቦችን የማልማትና አዳዲሶችን የመገንባት ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡

ከዚህም ባለፈ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ቁጥር እንዲጨምር፣ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ፣ ከቱሪዝም ዘርፍ የሚገኘው የውጪ ምንዛሪ ገቢ እንዲያድግ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያን በአፍሪካ ተመራጭና ተወዳዳሪ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ነባር መዳራሻዎች ዓለም አቀፍ ደረጃን ባሟላ መልኩ እንዲለሙ እየተደረገ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አዳዲስ መዳረሻዎችን በማስፋት፣ ቴክኖሎጂን ማዕከል ባደረገ መልኩ መስኅቦችን በማስተዋወቅ ማሕበረሱን ከቱሪዝም ዘርፍ በየደረጃው ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝም ነው የገለጹት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.