የበዓል ወቅት አመጋገብ ጥንቃቄ…
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የበዓላት ወቅት አመጋገብ ተገቢው ጥንቃቄ ካልተደረገበት ለጤና ችግር ሊዳርግ እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
በመሆኑም የበዓላት ወቅት አመጋገብን ጥንቃቄ የተሞላበት ማድረግ እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡
ምክንያቱም ቅባት የበዛበት ምግብ መመገብ ጨጓራን ለህመም የመዳረግ ዕድሉ ከፍተኛ ስለሚሆን ነው ይላሉ፡፡
ጥንቃቄ የጎደለው አመጋገብ ከሆነ÷ እንደ ሆድ መንፋት፣ የሆድ ቁርጠት፣ የጨጓራ ማቃጠል እና ሌሎች ህመሞችንም ሊያስከትል እንደሚችል ያስገነዝባሉ።
በመሆኑም በዓላትን የጤና መታወክ ሳያጋጥም ለማሳለፍ÷ የሚዘጋጀው ምግብ ንጽህናው እንዲጠበቅ እንዲሁም ምግቦች ቅባት የበዛባቸው እንዳይሆኑ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ይላሉ፡፡
በአመጋገብ ወቅትም ቀስ በቀስ ጨጓራን በማላመድ መሆን እንዳለበት ነው የሚመክሩት፡፡
ጣፋጭ ምግቦችን እና የአልኮል መጠጦችን ከልክ በላይ ባለመውሰድ እራስን እና ቤተሰብን ከህመም መጠበቅ እንደሚያስፈልግም ይገልጻሉ፡፡