የገና በዓል በላሊበላ በድምቀት እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ቤዛ ኩሉን ጨምሮ በተለያዩ ሐይማኖታዊ ሥርዓቶች እየተከበረ ነው።
የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቃ-ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ፣ ብጹዓን ሊቀ-ጳጳሳት፣ የክብር እንግዶች፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች እንዲሁም በርካታ ምዕመናን በበዓሉ አከባበር መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በቅዱስ ላሊበላ የሚከበረው የገና በዓል ከሐይማኖታዊ ሥርዓት ባለፈ በቱሪዝም መዳረሻነቱ ይታወቃል።