Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ መድን ስሑል ሽረን አሸንፏል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ12ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ መድን ስሑል ሽረን 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡

መሐመድ አበራ፣ ረመዳን የሱፍ እና መስፍን ዋሼ የኢትዮጵያ መድን ጎሎችን ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

የስሑል ሽረን ግብ ያስቆጠረው ደግሞ አሌክስ ኪታታ ነው፡፡

በአዳማ ሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው የዛሬ መርሐ-ግብር ሲቀጥል 12 ሠዓት ላይ መቻል ከሀድያ ሆሳዕና ይገናኛሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.