Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ክልሎች የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተለያዩ ክልሎች እና ርዕሳነ መስተዳድሮች የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት  በዓልን(ገና) በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል  ባስተላለፈው መልዕክት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ይህ በዓል የብሩህ ተስፋ መገለጫ  መሆኑን ጠቅሶ የክርስቶስ መወለድ ጨለማው በብርሃን የመሸነፉ ምልክት፤ የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ መሆኑን ገልጿል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር  ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)÷ በዓሉ ሲከበር  ያለ ልዩነት እርስ በርስ በመተጋገዝና በመደጋጋፍ፤ለሀገር ሰላምና አንድነት በጋራ በመቆም እንዲሁም እንደ ሀገር ያጋጠሙ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች እንዲፈቱ በመፀለይ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በተመሳሳይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው ባስተላለፉት መልዕክት÷በዓሉን ስናከብር በሁሉም መስክ በሚከናወኑ ስራዎች የኢትዮጵያን ትንሳኤ እዉን ለማድረግ መሆን አለበት ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ÷ “እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ” በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸው ህዝበ ክርስትያኑ የክርስቶስን አርዓያ በመከተል አንድነትን፣ፍቅርን እና ይቅርታን በማስቀደም ሰላማዊ እና የበለጸገች ሀገር ለመፍጠር መረባረብ አለበት ብለዋል፡፡

የሀረሪ ክልል እንዲሁ ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፎ የክልሉ ህዝብ እና መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉን በመደጋገፍ፣በወንድማማችነት መንፈስ እንዲያከብር ጥሪ አቅርቧል፡፡

የሲዳማ ክልል ባስተላለፈው መልዕክት÷የኢየሱስ ክርስቶስ የመወለዱ ምስጥር  የጥላቻና ያለመግባባት መንፈስ በፍቅርና በይቅርታ  ተቀይሮ ሰውና አምላኩ መልካም ግንኙነት እንዲኖራቸው ለማድረግ መሆኑን ገልጿል፡፡

በመሆኑም ያለፉትን ጉዳዮች በይቅርታ አልፈን በአዲስ ተስፋና ህብረት በፍቅር  ተደምረን የጋራ ቤታችን የሆነችውን  ኢትዮጵያ እንገንባ ብሏል፡፡

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ÷ ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈው÷ በዓሉን ሀገራዊ አንድነትን በሚያጠናክርና የክልሉን ሰላምና ልማት ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ ማክበር እንደመሚገባ ገልፀዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በበኩላቸው÷የእምነቱ ተከታዮች የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ሲያከብሩ በኃይማኖታዊ አስተምህሮው መሠረት በልደቱ ያገኙትን በረከትና መዳን፣ ትህትናና ፍቅር በተግባር በማሳዬት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የሲዳማ ክልል ባስተላለፈው መልዕክት÷የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የመወለዱ ምስጥር  የጥላቻና ያለመግባባት መንፈስ በፍቅርና በይቅርታ  ተቀይሮ ሰውና አምላኩ መልካም ግንኙነት እንዲኖራቸው ለማድረግ መሆኑን ገልጿል፡፡

ጥላቻና መገዳደልን አምላክ የማይወደው ጉዳይ ነው ያለው ክልሉ ÷በመሆኑም ያለፉትን ጉዳዮች በይቅርታ አልፈን በአዲስ ተስፋና ህብረት በፍቅር  ተደምረን የጋራ ቤታችን የሆነችውን  ኢትዮጵያን እንገባ ብሏል፡፡

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕከት አስተላልፈው÷በዓሉ በክልሉ የሰፈነዉን ሰላም ተጠቅሞ ህብረተሰቡ ፊቱን ወደ ልማት ባዞረበት ወቅት የሚከበር በዓል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በዓሉን ሀገራዊ አንድነትን በሚያጠናክርና የክልሉን ሰላምና ልማት ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ ማክበር እንደመሚገባ ገልፀው፣በዓሉ በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በበኩላቸው÷የእምነቱ ተከታዮች የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ሲያከብሩ በኃይማኖታዊ አስተምህሮው መሠረት በልደቱ ያገኙትን በረከትና መዳን፣ ትህትናና ፍቅር በተግባር በማሳዬት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የልደት በዓል ፈጣሪ ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር በተግባር የገለጠበት እና አንድነትም እውን የሆነበት በዓል በመሆኑ ይህንንም ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር መጠቀም እንደሚገባ ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.