Fana: At a Speed of Life!

ኤምባሲዎች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ተቀማጭነታቸውን ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል (ገና) የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በዚህም መሰረት የአሜሪካ፣ የብሪታኒያ እና የጀርመን ኤምባሲዎች ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በተመሳሳይ የተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ቢሮ እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ ሲል የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክቱን አስተላልፏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.