የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው፡፡
‘ከቃል እስከ ባህል’ በሚል መሪ ሀሳብ ፓርቲው አጠቃላይ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ በሁሉም ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ በሁለቱ የከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እንዲሁም በብልፅግና ፓርቲ የፌደራል ተቋማት አደረጃጀት ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በውይይቱ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ እና የኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን ባቀረበው ረቂቅ ሪፖርት ላይ ውይይት እየተካሄደባቸው ነው።
በቅድመ ጉባኤው ኮንፍረንሱ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ሌሎችም የሥራ ኀላፊዎች እየተሳተፉበት እንደሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ መረጃ ያመላክታል፡፡
የቅድመ ጉባኤ ውይይቶችና የአባላት ኮንፍረንስ እስከ ጉባኤው መዳረሻ ድረስ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።