ፕሬዚዳንት ታዬ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ኅልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ኅልፈተ ሕይዎት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ፡፡
ፕሬዚዳንቱ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልዕክት÷ “የተከበሩ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በማረፋቸው ብርቱ ሐዘን ተሰምቶናል” ብለዋል፡፡
ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን የተመኙት ፕሬዚዳንቱ÷ የአቶ ቡልቻ ነፍስ ፈጣሪ በአፀደገነት ያሳርፍ ሲሉ ገልጸዋል፡፡