Fana: At a Speed of Life!

ም/ጠ/ሚ ተመስገን በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሰላማዊ ትግል ውስጥ ትልቅ አስተዋፅዖ ማበርከታቸውን አውስተዋል፡፡

አቶ ቡልቻ ለሀገር ሁለንተናዊ ጥቅም የሰሩና ለችግሮችም እራሳቸውን የመፍትሔ አካል አድርገው ጽናትን ያሳዩ ሰው ነበሩ ብለዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በጉምቱው ፖለቲከኛ ሕልፈት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡

ፈጣሪ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑር ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ለቤተሰቦቻቸው፣ወዳጅ ዘመዶቻቸውና ኢትዮጵያዊውን መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.