Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በማረፋቸው የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡

በሚችሉት ሁሉ ሀገራቸውንና አፍሪካን ያገለገሉ፣ በአቋማቸው ጽኑ፣ ሕዝቦችን ለማቀራረብ የተጉ፣ እውነት ነው ብለው ያመኑትን የትምና መቼም የሚናገሩ ነበሩ ብለዋል፡፡

እንዲህ ዓይነት ብርቱ ሽማግሌዎችን ማጣት ጉዳቱ ለሀገር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይቀበላት ሲሉም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.