በትግራይ ክልል በመስኖ ሊለማ የሚችል መሬትን ለመጠቀም እየተሠራ ነው
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በትግራይ ክልል በመስኖ ሊለማ የሚችል መሬትን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል ፕሮጀክት ቀርፆ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር እየሠራ መሆኑን ገለፀ።
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ዴዔታ እንድሪያስ ጌታ (ዶ/ር) በሀገር አቀፍ ደረጃ ውኃን ማዕከል ያደረገ ልማትና ምርታማነትን በማሳደግ ለኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ እንዲኖረው በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አንስተዋል።
በትግራይ ክልል በመስኖ ሊለማ የሚችል ሰፊ መሬትና እምቅ አቅም እንዳለ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
በፌዴራል እና በክልሉ አቅም የሚከናወኑ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በማስተባበር የክልሉን የመስኖ ልማት አቅም ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
ከሚኒስቴሩ ጋር በመተባበር የመስኖ ልማትን ለማጠናከር ፕሮጀክቶችን ቀርጸው እንደሚሠሩ ያረጋገጡት ደግሞ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ኃላፊ እያሱ አብረሃ (ዶ/ር) ናቸው፡፡