አዳማ ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ12ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 0 ረትቷል፡፡
በአዳማ ሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ÷ የአዳማ ከተማን ጎሎች አሜ መሐመድ፣ ነቢል ኑሪ እና ኤሊያስ ለገሠ አስቆጥረዋል፡፡
በሌላ የጨዋታ መርሐ-ግብር በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመቐለ 70 እንደርታ ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡